Fana: At a Speed of Life!

ከ72 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የኮንትሮባንድ ዕቃ በቁጥጥር ስር ዋለ

አዲስ አበባ፣ሚያዝያ 27፣2012(ኤፍ.ቢ.ሲ) ባለፉት ስድስት ቀናት ከ72 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የኮንትሮባንድ ዕቃ በተለያዩ የጉምሩክ ኬላ ጣቢያዎች  በቁጥጥር ስር መዋሉን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ የተያዙባቸው ቦታዎች ጅግጅጋ፣ ድሬደዋ፣ ሀረር፣ ሞያሌ፣ አዳማ፣ ባህር ዳር፣ ዑመራ፣ ሞጆ፣ አዲስ አበባ፣ አዋሽ፣ ጅማ እና ሌሎች የጉምሩክ ኬላ ጣቢያዎች  መያዛቸው ተገልጿል።

ከተያዙት የገቢና ወጪ ኮንትሮባንድ ዕቃዎች ውስጥ ተሽከርካሽሪ፣ ጥራታቸው ያልተረጋገጡ መድሀኒቶች፣ ጭንብሎች (ማስኮች)፣ ምግብና የምግብ ነክ ቁሳቁሶች፣ የተሸከርካሪ መለዋወጫዎች፣ ቅሽር ቡና፣ አልባሳት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ የተለያዩ ዓይነት ጥይቶች፣ ሺሻና በገቢ ዕቃ አወጣጥ ታክስ ሳይከፈል ሊጭበረበር የነበሩ የተለያዩ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች  መሆናቸው ተመላክቷል፡፡

ከዚያም ባለፈ አንድ ድርጅት 23 ተሸከርካሪዎችና ማሽነሪዎችን ከቀረጥና ታክስ ነፃ አስገብቶ ከተፍቀደለት የኢንቨስትመንት መስክ ውጪ አገልግሎት ሲሰጥ በመገኘቱ በቁጥጥር ስር እንዲውል  መደረጉን ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ  ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!

https://t.me/fanatelevision

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.