ኢትዮጵያና ደቡብ አፍሪካ በወንጀል የተጠረጠሩ ግለሰቦችን አሳልፎ ለመስጠት የሚያስችል ስምምነት ተፈራረሙ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያና ደቡብ አፍሪካ በወንጀል የተጠረጠሩ ግለሰቦችን አሳልፎ ለመስጠት የሚያስችል ስምምነት ተፈራርመዋል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፣ የደቡብ አፍሪካ የዓለም አቀፍ ግንኙነቶችና ትብብር ሚኒስትር ዶክተር ናሌዲ ፓንዶር (ዶ/ር) እንዲሁም የሁለቱ አገራት ባለስልጣናት የተሳተፉበት አራተኛው የኢትዮ-ደቡብ አፍሪካ የጋራ የሚኒስትሮች ኮሚሽን ስብሰባ በአዲስ አበባ ተካሂዷል።
በዚህ ወቅት ሁለቱ ሀገራት በወንጀል የተጠረጠሩ ግለሰቦችን አሳልፎ ለመስጠት የሚያስችል ስምምነት ተፈራርመዋል።
ስምምነቱን የፍትሕ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ(ዶ/ር) እና የደቡብ አፍሪካ የዓለም አቀፍ ግንኙነቶችና ትብብር ሚኒስትር ናሌዲ ፓንዶር(ዶ/ር) ናቸው የተፈራረሙት።
ሁለቱ ሀገራት በስብሰባው ንግድ፣ ኢንቨስትመንት፣ ሳይንስ፣ ኢኖቬሽን፣ ትምህርት፣ ጤና፣ ባህልና በሌሎች በርካታ መስኮች የተፈራረሟቸውን የሁለትዮሽ ስምምነቶች ያሉበት የአፈጻጸም ደረጃ መገምገማቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!