የአዲስ አበባ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ከመሬት ይዞታ 5 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር ገቢ ሰበሰበ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በመሬት ዝግጅትና ማስተላለፍ ውጤታማ ሥራዎች ማከናወኑን የአዲስ አበባ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ አስታወቀ፡፡
የቢሮው ሃላፊ ቀነዓ ያደታ (ዶ/ር) ÷ቢሮው በበጀት ዓመቱ ከመሬት ይዞታ 5 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር ገቢ መሰብሰቡን ተናግረዋል፡፡
በተጨማሪም 144 ቦታዎችን በሊዝ ጨረታ በማስተላለፍ 3 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር ገቢ ማገኘቱን ነው የገለጹት፡፡
ለመዲናዋ የልማት ተነሺዎች ምትክ ቦታና ቤት መሰጠቱን ጠቁመው÷ 5 ቢሊየን የሚደርስ ካሣ መከፈሉንም ጠቅሰዋል፡፡
በሌላ በኩል ለልማትና ለተለያዩ ለማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎቶች የሚውሉ መሬት በማዘጋጀት በካቢኔ ውሳኔ ለአልሚዎች መተላለፋቸውን ገልፀዋል።
የመሬት ወረራ ከደንብ ማስከበርና ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር ሕዝቡን በማሳተፍ ወረራው ቢቀንስም አሁንም ችግሩን ሙሉ በሙሉ መቅረፍ እንዳልተቻለ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡