የሐይማኖት ተቋማት ጉባዔ መደበኛ ጉባዔውን እያካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ የሐይማኖት ተቋማት ጉባዔ 15ኛ መደበኛ ጉባዔውን ማካሄድ ጀምሯል።
በጉባዔው ላይ÷ የጉባዔው የበላይ ጠባቂ አባቶች እና የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
ጉባዔው በዛሬው እለት የ2015 በጀት አመት እቅድ አፈጻጸም እና የ2016 በጀት አመት እቅድ ላይ እንደሚወያይ ኢዜአ ዘግቧል፡፡
በተጨማም የስራና የሂሳብ ሪፖርት እንዲሁም አመታዊ ረቂቅ እቅድ ላይ ተወያይቶ ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል።