Fana: At a Speed of Life!

የፕላስቲክ ተረፈ ምርቶችን ወደ ግንባታ ግብዓትነት ለመቀየር የሚያስችል ፕሮጀክት ስምምነት ተፈረመ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የፕላስቲክ ተረፈ ምርቶችን ወደ ግንባታ ግብዓትነት በመቀየር እስከ 12 ሚሊየን ዶላር ማመንጨትና የውጭ ምንዛሪ ማዳን ለሚያስችል ፕሮጀክት ትግበራ የድጋፍ ስምምነት ተፈረመ፡፡

ስምምነቱን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር አማካሪ ሚኒስትር ዲዔታ ፎዚያ አሚን (ዶ/ር) እና የአዲል ቴክኖሎጂስና የኢኖቬሽን ማዕከል መስራችና ባለቤት አዲል አብደላ (ዶ/ር) ፈርመውታል።

ሚኒስቴሩ የቴክኖሎጂውን ጠቀሜታና ችግር ፈችነት በማመን የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ለፕሮጀክቱ አስፈላጊውን እገዛ እንዲያደርጉ ጠይቋል፡፡

የቴክኖሎጂ መትከያና የፕላስቲክ ማከማቻ ቦታ፣ ለፕሮጀክቱ አስፈላጊ የኢንዱስትሪ ምርቶችን ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገቡ ማድረግና ሌሎች ጉዳዮች ድርጅቱ የሚፈልጋቸው ድጋፎች መሆናቸው መጠቆሙን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

የሚኒስቴሩና የአዲል ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ማዕከል ስምምነት ፈጠራን እና ቴክኖሎጂን በመጠቀም የፕላስቲክ ተረፈ ምርቶች የሚፈጥሩትን የአካባቢ ብክለት ችግር ለመፍታት ያለመ ነው ተብሏል።

በኢትዮጵያ ከ380 ሺህ ሜትሪክ ቶን በላይ የፕላስቲክ ቆሻሻ ክምችት እንዳለና መልሶ መጠቀም የተቻለው 10 ከመቶ ብቻ መሆኑን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ገልጿል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.