በሶማሌ ክልል ጀረር ዞን በ201 ሚሊየን ብር ለሚገነቡ ፕሮጀክቶች የመሠረት ድንጋይ ተቀመጠ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሌ ክልል ጀረር ዞን ቢለቡር ወረዳ በ201 ሚሊየን ብር ለሚገነቡ የመንገድና የውሀ ፕሮጀክቶች የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሀመድ የመሠረት ድንጋይ አስቀመጡ፡፡
ከቢለቡር ወረዳ ደገሀቡር ከተማ ድረስ የሚገነባው የመንገድ ፕሮጀክት 43 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ሲሆን÷ ለፕሮጀክቱ ግንባታ 143 ሚሊየን ብር ወጪ ይደረግበታል ተብሏል።
ፕሮጀክቱ ለወረዳው ህዝብ የጎላ ጠቀሜታ እንደሚኖረው መገለጹን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡
በተመሳሳይ ርዕሰ መስተዳደሩ በቢለቡር ወረዳ በ58 ሚሊየን ብር ወጪ ለሚገነባው የንፁህ መጠጥ ውሀ ፕሮጀክት የመሠረት ድንጋይ አስቀምጠዋል።
ግንባታው በክልሉ የቆላማ አካባቢዎች የኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት አማካኝነት የሚካሄድ መሆኑም ተገልጿል፡፡