Fana: At a Speed of Life!

የላፕሴት ፕሮጀክትን ለአገልግሎት ክፍት ለማድረግ ሥራዎችን ማፋጠን እንደሚያስፈልግ ተጠቆመ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የላሙ ፖርት-ደቡብ ሱዳን-ኢትዮጵያ ትራንስፖርት (ላፕሴት) ፕሮጀክትን ለአገልግሎት ክፍት ለማድረግ ሥራዎችን ማፋጠን እንደሚያስፈልግ ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) የተመራ ልዑክ በኬንያ የሥራ ጉብኝት እያደረገ ነው፡፡

ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) ከጉብኝቱ ጎን ለጎን ከኬንያ የመንገድና ትራንስፖርት ካቢኔ ጸሐፊ ኦኔሲሙስ ኪፕቹምባ ሙርኮመን ጋር በሁለትዮሽ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።

በውይይታቸውም÷ የላሙ ፖርት-ደቡብ ሱዳን- ኢትዮጵያ ትራንስፖርት (ላፕሴት) ኮሪደር ልማትን ጨምሮ በቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን በኬንያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመላክታል፡፡

በዚሁ ወቅትም ዓለሙ (ዶ/ር) የላፕሴት ፕሮጀክት አጠቃቀምን ማፋጠን አስፈላጊ ስለመሆኑ በአጽንኦት ገልጸዋል፡፡

 

#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.