የአረንጓዴ አሻራ መርሐ -ግብር ለውሃ ሃብት ጥበቃ ካለው ፋይዳ አኳያ ሀገራት ሊተገብሩት እንደሚገባ ተጠቆመ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ እያካሄደችው ያለው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር ለዘላቂ የውሃ ጥበቃ ካለው ፋይዳ አኳያ ሀገራት በአርዓያነት ወስደው ሊተገብሩት እንደሚገባ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር ኢ/ር) ገለፁ።
የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር ኢ/ር) እንደተናገሩት ፥ ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ እየተተገበረ ያለው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር ለዘላቂ ውሃ ሀብት ጥበቃ ከፍተኛ ፋይዳ አለው።
የሚተከሉ ችግኞች ከአካባቢ ጥበቃ ፋይዳቸው ባሻገር ምንጮች እንዲጎለብቱ እና ለወንዞች ፍሰት መጨመር ጉልህ ሚና እንዳለው ጠቅሰው ፥ ይህም ከኢትዮጵያ አልፎ ለሌሎች ሀገራትም ፋይዳው የላቀ ነው ብለዋል።
በአጠቃላይ መርሐ ግብሩ ለአየር ንብረት ለውጥ መቋቋምና ለውሃ ሀብት ጥበቃ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ጠቅሰው፤ ሌሎች ሀገራት በአርዓያት ሊወስዱት እና ሊተገብሩት እንደሚገባ ተናግረዋል።
ሚኒስቴሩ ከተቋማት ጋር በመተባበር የውሃ ሀብት ጥበቃ ስራዎች ውጤታማ እንዲሆኑ የሚያስችሉ የጥናትና ምርምር ስራዎች ላይ እየሰራ መሆኑንም ነው ያነሱት።
ኢትዮጵያ በመጀመሪያው ምዕራፍ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር 25 ቢሊየን ችግኝ መትከሏ ይታወቃል።
በሁለተኛው ምዕራፍም 25 ቢሊየን ችግኞች ለመትከል የታቀደ ሲሆን ፥ ከዚህ ውስጥ በዘንድሮው ክረምት ከ 6 ነጥብ 5 ቢሊየን በላይ ችግኞችን ለመትከል ታቅዶ እየተሰራ እንደሚገኝ የዘገበው ኢዜአ ነው።
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!