Fana: At a Speed of Life!

ለ6 ‘ስታርትአፕ’ተመራቂዎች ለእያንዳንዳቸው የግማሽ ሚሊየን ብር ስራ መጀመሪያ ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከፍተኛ የፈጠራ ችሎታ ውጤት ላስመዘገቡ 6 ‘ስታርትአፕ’ ተመራቂዎች ለእያንዳንዳቸው እስከ 500 ሺህ ብር ስራ መጀመሪያ መነሻ ገንዘብ ድጋፍ መደረጉን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

ሚኒስቴሩ ከጃፓን ኢንተርናሽናል የትብብር ኤጅንሲ (ጃይካ) ጋራ በመተባበር ሲያከናውን በነበረው ኢትዮጵያ “ኤን አይ ኤን ጄ ኤ ፕሮጀክት” ከፍተኛ የፈጠራ ችሎታ ውጤት ላስመዘገቡ የኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ተቋማት ስራ መጀመሪያ መነሻ ገንዝብ ድጋፍ በማድረግ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በቦሌ ሳፋዬር ሆቴል አስመርቋል፡፡

ተመራቂውቹ ገበታ ማፕ፣ ሸማች፣ ፋይበር፣ ዲጂታል ሄልዝይ፣ ታይዋን እና ጉዞ የተባሉት ‘ስታርትአፕ’ ድርጅቶች ሲሆኑ÷ ላስመዘገቡት የላቀ ስኬት የገንዘብ ድጋፍ፣ እውቅና እና የምስክር ወረቀት ተሰጥቷቸዋል፡፡

በሚኒስቴሩ የኢኖቬሽን ልማት መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ ሰላምይሁን አድፈሪስ÷ በስራ እድል ፈጠራ፣ የህብረተሰቡን እድገት በማጎልበት ረገድ ስታርትአፖቹ ያላቸው አቅም ተስፋ ሰጪ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በኢትዮጵያ የNINJA ፕሮጀክት ተወካይ ሳቺኮ ሃራ በበኩላቸው÷ አጠቃላይ የፕሮጀክቱን ዓላማ፣ ፕሮግራሞችን፣ የነበረውን ሂደት በሚመለከት ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ተመራቂዎቹ ባለፉት አራት ወራት በሪኒው ካፒታል እና በጃፓን ሀገር የተለያዩ ስልጠናና ልምድ እንዲቀስሙ መደረጉንም የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

እንዲሁም የኢትዮጵያ የስታርትአፕ ስነ-ምህዳር ግንባታ ላይ ስላሉ ተግዳሮቶች እና እድሎች የፓናል ውይይት ተካሂዷል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.