Fana: At a Speed of Life!

አንዲት ላም 3 ጥጃዎችን በአንድ ጊዜ ወለደች

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ሸነን ኮሉ ወረዳ አንዲት ላም ሶስት ጥጃዎችን በአንድ ጊዜ መውለዷ ተሰምቷል፡፡

የላሟ ባለቤት ወይዘሮ አሻ አሊይ÷ ላሚቱ ከዚህ ቀደም በአንድ ጊዜ ሁለት ጥጃዎችን ወልዳ እንደነበር አስታውሰዋል፡፡

አሁን ላይም በአንድ ጊዜ ሶስት ጥጃዎችን መውለዷን ነው ወይዘሮ አሻ ያረጋገጡት፡፡

የተወለዱት ጥጃዎች እና ላሚቷ በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሚገኙም የወረዳው ኮሙኒኬሽን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት አስታውቋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.