Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ ያለው ኢንዱስትሪያላይዜሽን አበረታች ነዉ – ቻይናውያን ምሁራን

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ያለው ኢንዱስትሪያላይዜሽን አበረታች መሆኑን የቻይና ፔኪንግ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ገለፁ፡፡

ምሁራኑ ይህን የገለፁት ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የትራንስፎርሜሽንና ዋና ስራ አስፈፃሚ ፅ/ቤት ኃላፊ ፍፁም ከተማ ጋር በተወያዩበት ወቅት ነው።

ኃላፊው በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት፣ በኢንዱስትሪያላይዜሽን፣ በስራ እድል ፈጠራ፣ በኢንቨስትመንት ስበትና በሌሎች ተዛማጅ መስኮች የተከናወኑ ተግባራትና በዕቅድ የተያዙ ጉዳዮች ላይ ገለፃ አድርገዋል።

ኃላፊው አያይዘውም ፥ ምሁራኑ በዘርፉ ያላቸውን እምቅ አቅም በመጠቀም በተለያዩ ዓለምአቀፍ መድረኮች በማስተዋወቅ፤ ጥናትና ምርምሮችን መነሻ በማድረግ በኢትዮጵያ ያለውን አበረታች እንቅስቃሴ እንዲያግዙም ጥሪ አስተላልፈዋል።

ከዘርፉ ጋር በተያያዘ ያላቸውን ጥያቄዎችን አቅርበው ምላሽ የተሰጣቸው ምሁራኑ፤ ዩኒቨርሲቲያቸው አፍሪካ በተለይም ኢትዮጵያ ውስጥ ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ዘርፍ ጋር የተያያዙ ጥናቶችን እንደሚያደርግም ነው ምሁራኑ የገለጹት፡፡

በኢትዮጵያ ያሉት የኢንዱስትሪያላይዜሽን እድገቶች አበረታች መሆናቸውን ማንሳታቸውን ከኢንዱስትሪ ልማት ኮርፖሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ምሁራኑ በኢትዮጵያ በሚኖራቸዉ ቆይታ የሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክን ጨምሮ ሌሎችም መሰል የኢኮኖሚ ተቋማት ላይ የስራ ጉብኝት እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.