ፕሬዚዳንቱ የኢትዮጵያና የተባበሩት አረብ ኤምሬቶችን የሁለትዮሽ ግንኙነትን ለማሳደግ ቁርጠኝነታውን በድጋሚ አረጋገጡ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ፕሬዚዳንት ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን ሀገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ግንኙነትን ለማሳደግ ቁርጠኝነታውን በድጋሚ አረጋገጡ፡፡
በተባበሩት አረብ ኢምሬቶች የኢትዮጵያ አምባሳደር ዑመር ሁሴን የሹመት ደብዳቤያቸውን በቤተመንግስት በተካሄደ ሥነስርዓት ላይ ለፕሬዚዳንቱ አቅርበዋል፡፡
ፕሬዚዳንቱ የእንኳን ደህና መጡ መልዕክታቸውን ለአምባሳደሩ ገልጸው፤ መንግስታቸው ለአምባሳደሩ አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑንም አረጋግጠዋል።
አክለውም፥ ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ እና የኢትዮጵያ ህዝብ ላቀረቡላቸው መልካም ምኞትም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
በዚህ ወቅትም የሀገራቱን የሁለትዮሽ ግንኙነትን ለማጠናከር ጠንክሮ መስራት እንደሚያስፈልግም ነው የተናገሩት፡፡
ሀገራቸው እስካሁን በኢትዮጵያ ትኩረት ተሰጥቶ ያልተሰራባቸው ዘርፎች ላይ በመሰማራት የሁለትዮሽ ግንኙነቷን ለማሳደግ ያላትን ቁርጠኝነት ገልጸዋል፡፡
በዚህም ሀገሪቱ ፥ በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ፣ የኢንዱስትሪ፣ የግብርና እና የቱሪዝም ዘርፎችን ላይ ትኩረት አድርጋ እንደምትሰራ ገልጸዋል፡፡
#Ethiopia #saudiarabia #bilateral
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!