አየር መንገዱ ከአዲስ አፍሪካ ዓለም-አቀፍ ኮንቬንሽንና ኤግዚቢሽን ማዕከል ጋር ለመስራት ተስማማ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአዲስ አፍሪካ ዓለም-አቀፍ ኮንቬንሽን እና ኤግዚቢሽን ማዕከል አ.ማ. ጋር በጋራ ለመስራት ተስማማ፡፡
ስምምነቱ ቱሪዝምንና ንግድን በማቀላጠፍ የአገር ገጽታን የሚገነባ፣ ዘርፈ ብዙ እና ዓለም አቀፍ የንግድ ሁነቶችን ለማስተናገድ የሚያስችል ዘመናዊ የኮንቬንሽን እና ኤግዚቢሽን ማዕከል በአዲስ አበባ ለማቋቋም የሚያስችል የጋራ የኢንቨስትመንት ስምምነት ነው ተብሏል፡፡
የአዲስ አፍሪካ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽንና ኤግዚቢሽን ማዕከል የመጀመሪያ ዙር ግንባታ በ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ላይ የሚጠናቀቅ ሲሆን ኢትዮጵያ በዓመት 60 ዓለም አቀፍ ኤግዚቢሽኖችን እንድታዘጋጅ ያስችላታል።
የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ 12 ሺህ በላይ ካሬ ሜትር ላይ ያረፉ የኤግዚቢሽን ማሳያዎችና የተለያዩ ሁለገብ አዳራሾች እና ከአንድ ሺህ በላይ ታዳሚዎችን መያዝ የሚችል 7 ሺህ ካሬ ሜትር ስፋት ያለው አንፊ ቲያትርን ያጠቃለለ ነው።
ከአራት ቢሊዮን ብር በላይ የሚገነባው የኤግዚቢሽን ማዕከል፤ ግዙፍ የገበያ ሞልና በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ እንግዶችን በአንድ ቦታ ለማስተናገድ የሚያስችል አቅም አለው።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!