Fana: At a Speed of Life!

አቶ እንዳለው መኮንን ከዩናይትድ ኪንግደም ልዑክ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 16፣2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴኤታ እንዳለው መኮንን ከዩናይትድ ኪንግደም ልዑካን ቡድን አባላት ጋር ተወያይዋል፡፡

በውይይታቸውም÷ ዩናይትድ ኪንግደም ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባል ለመሆን የምታደርገውን ጥረት እና ብሔራዊ የጥራት መሰረተ ልማትን መደግፍ በምትችልበት ሁኔታ ላይ መክረዋል፡፡

ዩናይትድ ኪንግደም የዓለም ንግድ ድርጅት አባል ለመሆን እና የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ስምምነትን ለመተግበር በምታደርገው እንቅስቃሴ ቴክኒካዊ ድጋፎች እንደምታደርግ ልዑካኑ ገልፀዋል፡፡

በቀጣይም ነባራዊ ሁኔታዎች ላይ ጥናት በማድረግ እና ዝርዝር እቅድ በማዘጋጀት ወደ ተግባር ለመግባት ስምምነት  ላይ መደረሱን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.