Fana: At a Speed of Life!

ለ9 ሚሊየን ዜጎች አዳዲስ የስራ ዕድሎችን ለመፍጠር ታቅዷል – ፍጹም አሠፋ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ2016 እስከ 2018 በሚተገበረው ሁለተኛው ምዕራፍ የመካከለኛ ጊዜ ዕቅድ ለ9 ሚሊየን ዜጎች አዳዲስ የስራ ዕድሎችን ለመፍጠር መታቀዱን የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሠፋ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

በዕቅድ ዘመኑ በመጀመሪያው ምዕራፍ ዝቅተኛ አፈጻጸም የነበራቸው ዘርፎች የማካካሻ ዕቅድ እንዲያቅዱ፣ የተሻለ አፈጻጸም የነበራቸው ደግሞ ተጨማሪ ግብ እንዲኖራቸው ታቅዶ ወደ ስራ መገባቱንም ሚኒስትሯ ተናግረዋል።

የ10 ዓመት የልማት ዕቅድ የመጀመሪያው ምዕራፍ የመካከለኛ ጊዜ አፈጻጸምና የሁለተኛው ምዕራፍ የመካከለኛ ጊዜ ዕቅድ ግምገማ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዶ/ር) በተገኙበት ተካሂዷል።

ፍጹም አሠፋ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት ÷ ዓለም አቀፍና የሀገር ውስጥ ሰው ሰራሸና ተፈጥሯዊ ፈተናዎች በ10 ዓመት መሪ ዕቅድ አፈጻጸም ላይ አሉታዊ ጫና ማሳደራቸውን ጠቅሰዋል።

በውጭ ቀጥታ ኢንቨስመንትና በግብርናው ዘርፍ የተገኘው ውጤት ከዓለም አቀፍና ቀጣናዊ ዐውድ አንጻር ሲገመገምና በ10 ዓመት ዕቅድ ከተመላከተው ግብ አኳያ ሲታይ በተሻለ ደረጃ መፈጸሙን ገልጸዋል።

ዓለም አቀፍ ችግሮችን ተከትሎ የተከሰተው የዋጋ ንረት ትልቁ ተግዳሮት ቢሆንም በተሰሩ ተከታታይ ስራዎች መቆጣጠር መቻሉንም ጠቅሰዋል፡፡

የዓለም አቀፍ የልማት ተቋማት የፋይናንስ አቅርቦት በቂ አለመሆኑን ጠቅሰው÷ማህበረሰቡን በማስተባበር የፋይናንስ እጥረቱን በሀገር በቀል አማራጭ ለመተካት ጥረት መደረጉንም ነው ፍጹም አሠፋ (ዶ/ር) ያነሱት፡፡

ግብርና ተጨማሪ ግብ የተጣለበት ዘርፍ መሆኑን ገልጸው ÷ የቱሪዝም፣ ማዕድንና አምራች ዘርፎች ደግሞ የማካካሻ ዕቅድ እንዲኖራቸው መቃቀዱን አመላክተዋል፡፡

በዚህም የወርቅ የገበያ ድርሻ ከአራት ቶን ወደ 13 ቶን፣ የሀገር ውስጥ ምርቶችን የገበያ ድርሻ ወደ 46 በመቶ ለማሳደግ እንደታቀደ ተናግረዋል።

በጤና፣ በትምህርት፣ በውሃ፣ በኤሌክትሪክ አገልግሎት የዜጎችን ተጠቃሚነት ማሳደግ እንዲሁም የዋጋ ንረትን መቆጣጠር የቀጣይ ሦስት ዓመታት ትኩረቶች እንደሆኑም መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

#Ethiopia #10yeardevelopmentplan #ministryofplanninganddevelopment

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.