የኢትዮጵያ መንግስት እና ተመድ የሰብዓዊ ድጋፍ መልሶ ለማስጀመር ቁርጠኝነታቸውን ገለጹ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ መንግስት እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ለችግር ተጋላጭ ለሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች የሚደርሰውን ሰብዓዊ ዕርዳታ በአፋጣኝ ለማስጀመር የጋራ ጥረቶችን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስታወቁ።
የኢትዮጵያ መንግስት እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢትዮጵያ ቡድን በጋራ መግለጫ ማውጣታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል፡፡
የድርጅቱ በኢትዮጵያ ቋሚ ተወካይና የሰብዓዊ ጉዳዮች አስተባባሪ ራሚዝ አላክባሮቭ (ዶ/ር) እና የተመድ የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ተወካይ ማይክል ሳድን ጨምሮ ከድርጅቱ የኢትዮጵያ ቡድን ተወካዮች ጋር ውይይት ከተደረገ በኋላ ነው የጋራ መግለጫው የወጣው፡፡
በውይይቱም የኢትዮጵያ መንግስት እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አጋርነታቸውን ለማጠናከር ቁርጠኝነታቸውን ገልጸዋል፡፡
በኢትዮጵያ ሁሉን አቀፍ ዘላቂ ልማት ለማምጣት መስራታችንን እንቀጥላለን ሲሉም ነው በመግለጫቸው ያነሱት፡፡
ለአደጋ ተጋላጭ ለሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች ሰብዓዊ ድጋፍ በአፋጣኝ እንዲጀመር የጋራ ጥረታቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉም በመግለጫቸው አረጋግጠዋል፡፡
#Ethiopia #UN
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!