Fana: At a Speed of Life!

ግርማ አመንቴ(ዶ/ር) ከኢትዮጵያ የዛምቢያ አምባሳደር ጋር ተወያዩ

 

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ የዛምቢያ አምባሳደር ሮዝ ሳካላ ጋር ተዋያይተዋል፡፡

በዚህ ወቅት ሚኒስትሩ ÷ በኢትዮጵያ የምግብ ዋስትና እና ስርዓተ-ምግብን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የግብርናውን ዘርፍ ለማዘመን በሚደረገው ጥረትም አመርቂ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡

የግብርናውን ዘርፍ ለማሳደግ ተጀምረው እየተከናወኑ ያሉ የሌማት ትሩፋት ፕሮግራም፣ የበጋ መስኖ ስንዴ እና አረንጓዴ አሻራ ልማት ስራዎች አበረታች ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

በኢትዮጵያ የዛምቢያ አምባሳደር ሮዝ ሳካላ በበኩላቸው ÷ በኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ እየታየ ያለውን ለውጥ አድንቀዋል፡፡

ዛምቢያ በዘርፉ በልምድ ልውውጥ እና በሌሎችም ጉዳዮች ላይ ከኢትዮጵያ ጋር ለመስራት ፍላጎት እንዳላት መግለፃቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.