Fana: At a Speed of Life!

የኃይል ማመንጫ ግድቦች በቂ ውኃ መያዛቸው ተመላከተ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ለኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫነት የሚውሉ ሁሉም የውኃ ኃይል ማመንጫ ግድቦች በቂ ውኃ መያዛቸውን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኮርፖሬት ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ሞገስ መኮንን እንዳሉት÷ ጊቤ 3፣ ገናሌ ዳዋ እና ጊቤ 1 የውኃ ኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች ኃይል ማመንጨት የሚያስችላቸውን በቂ ውኃ ይዘዋል።

በተመሳሳይ መልካዋከና፣ አመርቲነሼ፣ ቆቃ እና ፊንጫ የኃይል ማመንጨት ሥራቸውን ለማከናወን የሚያስችል ውኃ መያዛቸውን ነው አቶ ሞገስ ያስታወቁት።

እንደ ጊቤ 2፣ አዋሽ 2 እና 3 ያሉና ሌሎች የኃይል ማመንጫዎች ኃይል ለማመንጨት የሚያስችላቸው በቂ ውኃ እየገባ መሆኑን ነው የጠቆሙት፡፡

በያዝነው የክረምት ወቅት ውኃ ያልያዘ የኃይል ማመንጫ አለመኖሩንም አስረድተዋል።

በዮሐንስ ደርበው

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.