ቻይና ለኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ነፃ የትምህርት ዕድል ሠጠች
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና ለኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ነፃ የትምህርት ዕድል ሠጠች፡፡
የቻይና መንግስት በሠጠው ነፃ የትምህርት ዕድል በፈረንጆቹ 2023/2024 ትምህርት ለመጀመር አሸናፊ የሆኑ 26 ተማሪዎችም አዲስ አበባ በሚገኘው የቻይና ኤምባሲ ሽኝት ተደርጎላቸዋል።
በሽኝት መርሐ- ግብሩ ላይ የተገኙት በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ዣዎ ዚዩአን ÷ ሀገራቸው በኢትዮጵያ የሚደረገውን የእውቀትና ቴክኖሎጂ ሽግግር በዘላቂነት እንደምትደግፍ ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ እና ቻይና መካከል ያለው ሁሉን አቀፍ ስትራቴጂያዊ ትብብርም የጋራ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አምባሳደሩ መናገራቸውን ከኤምባሲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በሽኝት መርሐ- ግብሩ ÷ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሥራ ኃላፊዎችና ቀደም ሲል በቻይና ትምህርታቸውን ተከታትለው የተመለሱ ምሁራን መገኘታቸውን ከኤምባሲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡