ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሴቶች ማራቶን ውጤት ላስመዘገቡ አትሌቶች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ
አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 20 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሴቶች ማራቶን ውጤት ላስመዘገቡ አትሌቶች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው÷ “በቡዳፔስት 2023 የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በሴቶች ማራቶን ወርቅ እና ብር ላስመዘገቡ ሴት አትሌቶቻችን ያለኝን አድናቆት እገልጣለሁ” ብለዋል።
እንኳን ደስ አላችሁ፤በአንድነት በመሥራት ብዙ ተጨማሪ ድንቅ ድሎችን ማሳካት እንችላለን ነው ያሉት በመልዕክታቸው፡፡