Fana: At a Speed of Life!

የመኪና ባትሪና የአሉሚኒየም ቁርጥራጮችን ወደ ምርት መቀየር የሚያስችል ፋብሪካ ሊገነባ ነው

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)የመኪና ባትሪ እና የአሉሚኒየም ቁርጥራጮችን መልሶ ጥቅም ላይ እንዲውሉ የሚያደርግ ፋብሪካ ሊገነባ መሆኑን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

ሥምምነቱን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር እና የሕንድ የኢንዱስትሪ ማሽነሪዎች አምራች ኩባንያ ፈርመውታል፡፡

የሚገነባው ፋብሪካ ፥ ባትሪዎችንና ቁርጥራጮችን ወደ ተለያዩ ምርቶች ቀይሮ ወደ ውጭ በመላክ የውጨ ምንዛሬ ለኢትዮጵያ የሚያስገኝ ነው ተብሏል፡፡

በሥምምነት ፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ በመገኘት መልዕክት ያስተላለፉት የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ ታረቀኝ ቡሉልታ ÷ ኩባንያዎቹ ያደርጉት የሥራ ሥምምነት ለአምራች ኢንዱስትሪው ዕድገት ትልቅ ሚና ያለው መሆኑን ገልጸዋል።

ለሥምምነቱ ዕውን መሆንም ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ አሥፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ነው የገለጹት፡፡

በሥምምነቱ የአዋሽ ባንክ ተወካዮች መገኘታቸውንና ፋብሪካውን ዕውን ለማድረግ በሚደረገው ሂደት ባንኩ የፋይናንስ ድጋፍ እንደሚያደርግ መግለጻቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.