ኢትዮጵያ እና ናይጄሪያ በተለያዩ መሥኮች እንሰራለን አሉ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)ኢትዮጵያ እና ናይጄሪያ በንግድ፣ ኢንቨስትመንት እና ጸጥታ ጉዳዮች ግንኙነታቸውን ይበልጥ ለማጠናከር ዝግጁ መሆናቸውን አስታወቁ፡፡
በናይጄሪያ የኢትዮጵያ አምባሳደር አዋል ዋግሪስ መሐመድ የሹመት ደብዳቤያቸውን ለናይጄሪያ ፕሬዚዳንት ቦላ አሕመድ ቲኑቡ አቅርበዋል።
በዚህ ወቅትም ፥ የሀገራቱ ታሪካዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የበለጠ መጠናከር በሚችልበት ሁኔታ ላይ መምከራቸውንም ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በናይጄሪያ የኢትዮጵያ አምባሳደር አዋል ዋግሪስ ሞሐመድ ÷ ኢትዮጵያ ከተለያዩ ሀገራት ጋር ያላትን የሁለትዮሽና የባለ-ብዙ ወገን ትብብር የበለጠ ለማሳደግ ቁርጠኛ መሆኗንም ገልጸዋል።
ፕሬዚዳንቱ በበኩላቸው ፥ ሀገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር በንግድ፣ ኢንቨስትመንት እና ጸጥታ ጉዳዮች ላይ ያላትን ግንኙነት ለማጠናከር ዝግጁ መሆኗን አረጋግጠዋል።