በእስራኤል ጥገኝነት የሚጠይቁ ኤርትራውያን ከፖሊስ ጋር ተጋጭተው በርካቶች መቁሰላቸው ተነገረ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቴል አቪቭ የኤርትራ ኤምባሲ ያዘጋጀውን ዝግጅት በመቃወም የወጡ በመቶ የሚቆጠሩ ጥገኝነት ጠያቂ ኤርትራውያን ከፖሊስ ጋር ተጋጭተው በርካቶች መቁሰላቸው ተነገረ።
በግጭቱ የእስራኤል ፖሊስ መኮንኖችን ጨምሮ 140 ሰዎች መቁሰላቸውን እና ቢያንስ ሶስት ተቃዋሚ ሰልፈኞች ከፖሊስ በተተኮሰ ጥይት ተመተው ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰባቸው ተገልጿል፡፡
የእስራኤል ፖሊሶች ሁከቱን ለማስቆም ጥረት ሲያደርጉ ተቃዋሚዎቹ ብረት፣ ዱላ፣ ድንጋይ እና የተለያዩ ነገሮችን ሲወረውሩ ነበር ሲል ዘ ኒው አረብ ዘግቧል።
በተመሳሳይም በአውሮፓ እና በሰሜን አሜሪካ የሚገኙ የኤርትራ ዲያስፖራዎች የ30ኛ ዓመት የነፃነት በዓል ለማክበር ፌስቲቫሎች ሲዘጋጁ የነበሩ ቢሆንም በኤርትራ መንግስት ተቃዋሚዎች እና ደጋፊዎች መካከል በሚፈጠር ግጭት ሲስተጓገሉ ተስተውሏል።