Fana: At a Speed of Life!

የተሻለ አገልግሎት በመስጠት የህብረተሰቡን ፍላጎት ለማሟላት ተዘጋጅተናል – የአፋር የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በተቋማቸው የተሻለ አገልግሎት በመስጠት የህብረተሰቡን ፍላጎት ለማሟላት መዘጋጀታቸውን በአፋር ክልል የሚገኙ የተለያዩ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ሃላፊዎች ተናገሩ።

በክልሉ የአገልጋይነት ቀን “ኢትዮጵያን እናገልግል” በሚል መሪ ሐሳብ የሴክተር መስሪያ ቤቶች ሥራ ሃላፊዎችና ሠራተኞች በተገኙበት በተለያዩ ተግባራት ተከብሯል።

ከሴክተር መስያቤቶች መካከል የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሃላፊ አቶ አህመድ አብዱልቃድር እንዳሉት÷ አገልግሎትን ማዘመንና ሁሉም ሠራተኛ የአገልጋይነት ባህሪ እንዲላበስ ማድረግ ይገባል።

ህዝብን በቅንነት ማገልገል ክብር መሆኑን የጠቆሙት ሃላፊው÷ በተቋማቸው የህብረተሰቡን ፍላጎት ያሟላ አገልግሎት ለመስጠት በቁርጠኝነት እንደሚሰራ ተናግረዋል።

የአፋር ክልል የመንገድ ልማት እና ትራንስፖርት ቢሮ የትራንስፖርት ዘርፍ ምክትል ሃላፊ ወይዘሮ መዲና ማህሙድ በበኩላቸው ÷ በአገልግሎት አሰጣጡ ላይ የሚስተዋል ክፍተቶችን ፈትሾ ጥራት ያለው አገልግሎት ለመስጠት ይሰራል ብለዋል፡፡

የሠመራ ሎጊያ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አብዱ ሙሳ÷ ከተለያዩ ሴክተር ተቋማት ጋር ተናበው በመስራት ለህብረተሰቡ የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት እንደሚሰራ ገልጸዋል።

በክልሉ የመንገድ ልማት እና ትራንስፖርት ቢሮ የመንገድ ፈንድ ዘርፍ ምክትል ሃላፊ አቶ ሁሴን ቦልኮ÷የህብረተሰቡን ፍላጎት ያሟላ አገልግሎት መስጠት እንደሚገባ መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ለእዚህም በየደረጃው ያለው አመራርና ሠራተኛው የህዝብ አገልጋይነት መንፈስ መላበስ እንዳለበት ጠቁመው÷  ለሁሉም አገልግይነትን የሚያጎናጽፈውን ክብር ማስገንዘብ ይገባል ብለዋል።

በመንገድ አገልግሎቱ ለህብረተሰብ ምቹና ጥራት ያለው አገልግሎት መስጠት እንዲቻል በዘርፉ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት ይሰራል ሲሉም አቶ የሱፍ አረጋግጠዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.