Fana: At a Speed of Life!

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ከ3 የስኳር ፋብሪካዎች ጋር ተፈራረመ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች አገልግሎት ከ3 ግዙፍ የስኳር ፋብሪካዎች ጋር የውል ስምምነት ተፈራርሟል፡፡

ስምምነቱን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ እና የሶስቱ የስኳር ፋብሪካ ስራ አስኪያጆች ፈርመውታል፡፡

ስምምነቱ ፋብሪካዎቹ ያጋጠማቸውን የምርት መቀነስ፣ የማሽነሪዎች ብልሽት እድሳትና ቅያሪ እንዲሁም ማስፋፊያዎቹን ታሳቢ በማድረግ በጥናት የተደገፈ ለፋይናንስ ምንጭ የሚሆን ዶክመንት የማዘጋጀትና ፋብሪካዎቹን ውጤታማ የሚያደርግ ጥናት ለመስራት የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡

የስምምነት ፊርማ ያደረጉት የስኳር ፋብሪካዎች በሚኒስትሮች ምክር ቤት ራሳቸውን ችለው እንዲቋቋሙ በተወሰነላቸው መሰረት በሙሉ አቅማቸው ወደስራ ለመግባት እየሰሩ እንደሆነ መጠቀሱን የኮርፖሬሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡

የኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች አገልግሎት በጥናትና ማማከር ላለፉት 40 ዓመታት በላይ የተለያዩ ግዙፍ ሀገራዊ ፕሮጀክቶችን እውን ያደረገ ተቋም ነውም ተብሏል፡፡

በተመሳሳይ የማካካሻ (Remedial) ትምህርት ፈተና ከመስከረም 7 እስከ 10 ቀን 2016 ዓ.ም እንደሚሰጥ የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

ፈተናው የሚሰጠው የማካካሻ ትምህርታቸውን አጠናቅቀው ከሰኔ 26 እስከ 30 ቀን 2015 ዓ.ም የተሰጠውን የማዕከል ፈተና ላልወሰዱ ተማሪዎች መሆኑን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡

ፈተናው በ30 የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የሚሰጥ መሆኑም ተገልጿል።

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.