Fana: At a Speed of Life!

የአምራችነት ቀንን አስመልክቶ ሚኒስትሮች ፋብሪካ ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) “ከሸማችነት ወደ አምራችነት” በሚል መሪ ሃሳብ እየተከበረ የሚገኘውን የአምራችነት ቀንን አስመልክቶ ሚኒስትሮች በፋብሪካ ተገኝተው ጉብኝት አድርገዋል፡፡

የኢንዱስትሪ፣ የስራ እና ክህሎት፣ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር፣ የማዕድን እና ገቢዎች ሚኒስቴር ሚኒስትሮች፣ ሚኒስትር ዴዔታዎችና የተቋማቱ አመራሮች ናቸው የፋብሪካ ጉብኝት ያደረጉት፡፡

በጉብኝታቸውም፥ አምራች ኢንዱስትሪዎቹ ያሉባቸውን ችግሮች በዘላቂነት ለመፍታት በሚያስችሉ የመፍትሄ ሃሳቦች ዙሪያ መመካከራቸውን ከኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

በዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮች በተቋማት ቅንጅታዊ አሰራር ለመፍታት የሚያስችል ጉብኝት እንደነበር የገለጹት የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ ታረቀኝ ቡሉልታ ናቸው፡፡

#Ethiopia #Industry

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.