Fana: At a Speed of Life!

የአምራች ተቋማትን ለማበረታታት እየተሠራ ነው – የሐረሪ ክልል አመራሮች

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) መንግስት የአምራች ተቋማትን ለማበረታታት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ የተለያዩ ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን ሐረሪ ክልል አመራሮች ተናገሩ፡፡

የአምራችነት ቀን በሐረሪ ክልል “ከሸማችነት ወደ አምራችነት” በሚል መሪ ሐሳብ በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብሯል፡፡

ዕለቱን በተመለከተም የሐረሪ ክልል ምክር ቤት አፈጉባኤ ሱልጣን አብዱሰላም እና የሐረሪ ክልል የኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ ኃላፊ ሰሚራ ዩሱፍን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች የተለያዩ የማምረቻ ተቋማትን ጎብኝተዋል፡፡

በጉብኝቱ ላይ አፈ ጉባኤ ሱልጣን ባደረጉት ንግግር÷ መንግስት የአምራች ተቋማትን ለማበረታታት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ የተለያዩ ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በብዛትና በጥራት በማምረት ከሀገር ውስጥ ፍጆታ ባለፈ አምራቾች የውጪ ምንዛሬ እንዲያስገኙ በሚደረግላቸው ድጋፍ አበረታች ውጤት እየተገኘ መሆኑንም ነው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የተናገሩት፡፡

ወይዘሮ ሰሚራ ዩሱፍ በበኩላቸው÷ ፋሪካዎችና አምራች ተቋማት ያሉባቸውን ችግሮች በዘላቂነት በመፍታት ውጤታማ እንዲሆኑ በመንግስት በኩል እየተሰራ መሆኑን አመላክተዋል፡፡

በመቅደስ ደረጀ

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.