Fana: At a Speed of Life!

በጎንደር ጊዜያዊ ማቆያ የሚገኙ ተጠርጣሪዎች የሰብዓዊ መብት አያያዙ ጥሩ ነው አሉ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰሜን ምዕራብ አማራ ኮማንድ ፖስት በጎንደር ከተማ ጊዜያዊ ማቆያ የሚገኙ ተጠርጣሪዎች የሰብዓዊ መብት አያያዙ በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ተናገሩ።
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርማሪ ቦርድ በስፍራው ባደረገው ጉብኝት ተጠርጣሪዎች አስፈላጊ አገልገሎቶችን እያገኙና ሰብዓዊ አያያዙም ጥሩ መሆኑን ማረጋገጡን ገልጿል።
መርማሪ ቦርዱ በአማራ ክልል ተፈጥሮ በነበረው ሁከት በወንጀል ተጠርጥረው በጎንደር ከተማ ጊዜያዊ ማቆያ የሚገኙ ተጠርጣሪዎችን ጎብኝቷል፡፡
በማቆያው የሰብዓዊ መብት አያያዛቸው በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ የገለጹት ተጠርጣሪዎቹ የወንጀል ምርመራ ሂደቱ እንዲፋጠንላቸው ጠይቀዋል፡፡
በማቆያው የሚገኙ የፖሊስ አባላት ስነ ምግባርን በተላበሰ መልኩ ኃላፊነታቸውን እየተወጡ መሆናቸውንም ነው ተጠርጣሪዎቹ ለኢዜአ የገለጹት፡፡
ህክምና፣ የመጠጥ ውሃ፣ የመኝታ፣ የመታጠቢያና ሌሎች አገልግሎቶች እየቀረቡ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
ቤተሰቦቻቸው ተመላልሰው እየጠየቋቸው መሆኑንም ነው ያመላከቱት፡፡
የኮማንድ ፖስቱ ሰብሳቢ ብርጋዴር ጀነራል ዋኘው አለሜ እንዳሉት÷ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ከዋሉ ጊዜ ጀምሮ የሰብዓዊ መብታቸው እንዲጠበቅ ክትትል እየተደረገ ነው፡፡
ተጠርጣሪዎች እንዲሟላ የጠየቁትን ጉዳይም ለሚመለከተው አካል በማሳወቅ አፋጣኝ መፍትሄ እንዲያገኙ ይደረጋል ተብሏል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.