መሠረታዊ የኢኮኖሚ ለውጥ ለማምጣት ሰፊ ሥራ ጀምረናል – አቶ ሽመልስ አብዲሳ
አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) መሠረታዊ የምጣኔ ሐብት ለውጥ ለማምጣት ሰፊ ሥራ መጀመሩን የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ገለጹ፡፡
የተጀመሩት ሥራዎች እና እርምጃዎች ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት መጀመራቸውንም ነው አቶ ሽመልስ የተናገሩት፡፡
“የምጣኔ ሐብታችን ዋልታ የሆነውን ግብርና ከተለመደው ኋላ ቀር አሠራር በማውጣት ወደ ሜካናይዜሽን ግብርና ለማስገባት ጉዞ ከተጀመረ ቆይቷል” ሲሉ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል፡፡
ዘርፉን ለማዘመንና እና ከፍተኛ ስኬት ለማስመዝገብ የተለያዩ ኢኒሼቲቮችን በመቅረጽ እየተሠራ ነው ብለዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!