Fana: At a Speed of Life!

በሥነ ምግባር የታነጸ ትውልድ ለመፍጠር በትኩረት መስራት ይገባል – ሳሙኤል ዑርቃቶ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ ፣ ጳጉሜን 5 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሥነ ምግባር የታነጸና ሙስናን የሚጸየፍ ትውልድ ለሀገረ መንግስት ግንባታ ወሳኝ በመሆኑ ቀዳሚ ትኩረት ተሰጥቶት ሊሰራበትእንደሚገባ የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ገለጸ።

የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽነር ሳሙኤል ዑርቃቶ (ዶ/ር) እንደገለጹት÷ሙስና ከቤተሰብ እስከ ሀገር የሚያፈርስ አደገኛና ውስብስብ ችግር በመሆኑ ከመሰረቱ ለመንቀል ብርቱ ጥረት ይጠይቃል።

ሙሰኞችን በመከላከልና የተጠያቂነት ስርዓት በማስፈን ብቻ ሳይሆን የሙሰኝነት ተግባርን የሚጸየፍ በስነ ምግባር የታነጸ ትውልድ ግንባታ ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚጠይቅ አንስተዋል።

በሥነ ምግባር የታነጸ፣ ሙስናን የተጸየፈ ትውልድ መገንባት ለሀገረ መንግስት ግንባታ ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ግብረ ገባዊነት የኅብረተሰብና የሀገር መሠረት በመሆኑ በትምህርትና ስልጠና ረገድ ከቅድመ መደበኛ ጀምሮ የማህበረሰቡ የሥነ ምግባር እና የሞራል ትምህርቶች እንዲሰጡ የሪፎርም ስራዎች መሰራታቸውን ገልጸዋል።

ሙስና ሀገርን የሚበላና አንጡራ ሀብቷን እየቦረቦረ በመሆኑ ሙስናን የመዋጋት ጉዳይ የጋራ አጀንዳ ነው ብለዋል።

በዚህም የሃይማኖትና የባህል ተቋማትን ጨምሮ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በሀገር ሞራል እና በሥነ ምግባር እሴቶች ላይ በቅንጅት እንዲሰሩ መጠየቃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.