Fana: At a Speed of Life!

በሶማሌ ክልል ድጋፍ ለሚሹ ከ83 ሺህ በላይ ዜጎች እርዳታ እየተሰራጨ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሌ ክልል ድጋፍ ለሚሹ ከ83 ሺህ በላይ ዜጎች የዕለት ደራሽ የምግብ እርዳታ እየተሰራጨ መሆኑን የክልሉ የአደጋ ስጋት አመራር ቢሮ አስታውቋል።

የቢሮው ሃላፊ አቶ አሕመድ ያሲን እንደገለጹት÷ በተለያዩ አካባቢዎች ለተፈናቀሉ እና ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች የዕለት ደራሽ የምግብ እርዳታ ማሰራጨት ተጀምሯል፡፡

ድጋፉን ጅግጅጋ፣ ዳዋ እና ጎዴ ከተሞች ከሚገኙ የእርዳታ መጋዘኖች ወደ ሁሉም የክልሉ ዞኖች ማጓጓዝ መጀመሩን ነው የተናገሩት፡፡

በዚህም ከ83 ሺህ በላይ የሚሆኑ ዜጎች የዕለት ደራሽ የምግብ ድጋፉ ተጠቃሚ እንደሚሆኑ መግለጻቸውን የክልሉ መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.