የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ማስጠበቅ የጋራ አጀንዳችን ነው – ምክር ቤቱ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ማስጠበቅ፣ የልማትና የሰላም ግንባታ ጉዳይ የጋራ ሀገራዊ አጀንዳችን ሆኖ ይቀጥላል ሲል የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ገለጸ፡፡
የምክር ቤቱ ሰብሳቢ ደስታ ዲንቃ እንዳሉት÷ የፖለቲካ አስተሳሰብ ልዩነቶች ቢኖሩንም በሀገራዊ ልማት፣ ዘላቂ ሰላምና አንድነታችንን ማስጠበቅ ላይ ልንደራደር አይገባም፡፡
በተለይም የፖለቲካ ፓርቲዎች በሀገራዊ የልማት ዕቅዶች ላይ አጋዦች እንጂ ፈፅሞ የአፍራሽነት ሚና ሊኖረን አይገባም ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
የቀጣይ ሥራዎቻችን ከኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ባሻገር ለማኅበራዊና የፖለቲካ መስተጋብሮች ቁርኝት ይበልጥ አጋዥ ሆነው ሊቀጥሉ ይገባል ብለዋል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!