Fana: At a Speed of Life!

850 አምቡላንሶች በመላ ሀገሪቱ ተከፋፈሉ

አዲስ አበባ፣ግንቦት 6፣2012(ኤፍ.ቢ.ሲ) 850 አምቡላንሶች በመላ ሀገሪቱ መከፋፈላቸውን በጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

በጤና ሚኒስቴር የንብረት አስተዳደርና ጠቅላላ አገልግሎት ዳሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ እስክንድር ላቀው÷ ሚኒስቴሩ በ2010 ዓ.ም በእቅድ ይዞ በሀገሪቱ ያለውን የአምቡላንስ ክፍተት ለሟሟላት ከከልሎች ጋር በመወያየት በሶስት ዙር የ3 ሺህ 14 አምቡላንሶች ግዢ መፈጸሙን ተናግረዋል።

መንግስትም የውጪ ምንዛሬ በማመቻቸት እና ከቀረጥ ነጻ እንዲገቡ በመፍቀድ በጠቅላላው ከ 3 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ  እንደተደረገባቸውም  ገልጸዋል።

አምቡላሶቹም  በክልል፣ በዞን፣ በወረዳ፣ በከተማ አስተዳደሮችና በዩኒቨርሲዎች ተሰራጭተው የህሙማን ቅብብሎሽን በማቀላጠፍ የድንገተኛ አደጋና የእናቶችን ሞት ለመቀነስ አገልግሎት ላይ የሚውሉ ናቸውም ነው ያሉት።

በመሆኑም  ቀደም ሲል 2 ሺህ 116 አምቡላንሶች የተሰራጩ ሲሆን ቀሪዎቹ 850  በዛሬው እለት ለአማራ ክልል 135 እና ለፌደራል ፖሊስ 50 አምቡላንሶች በተደረሰው ስምምነት መሰረት የተረከቡ ሲሆን÷ቀሪዎቹ ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች በቀጣይ ቀናት እንደሚረከቡም ነው የገለጹት።

አቶ እስክንድር አያይዘውም በዚህ ወቅት አምቡላንሶቹ መድረሳቸው ኮቪድ 19 የመከላከሉን ስራ ያግዛል ያሉ ሲሆን ÷ አምቡላንሶቹ ከፍተኛ የሀገር ሀብት የፈሰሰባቸው በመሆኑ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ለታለመለት አላማ ብቻ በማዋልና ተገቢውን ወቅታዊ ጥገና በማድረግ በባቤትነት ስሜት ሊገለገሉበት ይገባል ማለታቸውን ከጤና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል ።

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.