Fana: At a Speed of Life!

የአፍሪካ ቀንድ ኢኒሼቲቭ የሚኒስትሮች ስብሰባ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው

 

አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ ቀንድ ኢኒሼቲቭ የሚኒስትሮች ስብሰባ በአዲስ አበባ በዛሬው እለት መካሄድ ጀምሯል።

እየተካሄደ ባለው 18ኛው የአፍሪካ ቀንድ ኢኒሼቲቭ የሚኒስትሮች ስብሰባ የኢኒሼቲቩ ሊቀመንበር እና የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ ተገኝተዋል።

የአውሮፓ ሕብረት ዓለም አቀፍ የትብብር ኮሚሽነር ጁታ ኡርፒላይነን፣ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) ዋና ፀሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር)፣ የኢኒሼቲቩ አባል ሀገራት ሚኒስትሮችና የልማት አጋር ተወካዮችም ታድመዋል።

የአፍሪካ ቀንድ ኢኒሼቲቭ በፈረንጆቹ 2019 ማብቂያ በአፍሪካ ቀንድ የፋይናንስ ሚኒስትሮች የተቋቋመ መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በአፍሪካ ልማት ባንክ፣ የዓለም ባንክ እና አውሮፓ ሕብረት ድጋፍ የተቋቋመው ኢኒሼቲቭ ቀጣናዊ ትብብርን ማጠናከር እንዲሁም በልማት ስራዎች በተለይም በመሰረተ ልማት፣ ንግድ፣ አቅም ግንባታ መስኮች የተሻሉ ውጤቶችን ማምጣት ዋነኛ የትኩረት አጀንዳ አድርጎ ይሰራል።

ኢኒሼቲቩ ኢትዮጵያን፣ ኬንያን፣ ሶማሊያን፣ ጂቡቲን፣ ኤርትራን፣ ሱዳን እና ደቡብ ሱዳንን በአባልነት ያቀፈ ሲሆን÷ ከየካቲት 2015 ዓ.ም ጀምሮ የአፍሪካ ቀንድ ኢኒሼቲቭን ኢትዮጵያ በሊቀመንበርነት እየመራች ትገኛለች።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.