Fana: At a Speed of Life!

ኖርዌያዊው ደራሲ ጆን ፎሴ በስነ ፅሁፍ ዘርፍ የኖቤል ሽልማትን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኖርዌያዊው ደራሲ ጆን ፎሴ የ2023ቱን የስነ ፅሁፍ ዘርፍ የኖቤል ሽልማት አሸንፏል፡፡

ደራሲው መናገር የማይችሉ ሰዎች በድምጽ ሊገነዘቧቸው የሚችሉ የፈጠራ ተውኔቶችን በመፃፉ ነው በዘርፉ የኖቤል ሽልማትን ማሸነፍ የቻለው፡፡

የዘርፉ አወዳዳሪ ዳኞች÷ ደራሲው በአለማችን ከሚገኙ ተፅዕኖ ፈጣሪ ፀሃፌ ተውኔቶች አንዱ መሆኑን ገልፀው፤ የፃፋቸው ባለ ድምጽ ተውኔቶች በአለም ዓቀፍ ደረጃ ተቀባይነታቸው እየጨመረ እንደሚሄድ ተናግረዋል።

ጆን ፎሴ በአጠቃላይ የስነ ፅሁፍ ስራዎቹ ተውኔቶችን፣ ልብ ወለዶችን፣ ግጥሞችን፣ ድርሰቶችን፣ ትርጉሞችን እና የህጻናት መጽሃፎችን ጨምሮ የተለያዩ ዘውጎችን መፃፉ ተመላክቷል፡፡

የስነ ፅሁፍ ዘርፍ ሽልማት 4ኛው የዓመቱ የኖቤል ሽልማት ዘርፍ ሲሆን ቀደም ሲል በሳይኮሎጂ ዘርፍ፣ በመድሃኒት ቅመማ እና በሳይንስ ዘርፎች አሸናፊዎች መለየታቸውን ኒውስ ሌተርስ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.