ኢትዮጵያ የዲጂታል መታወቂያ ለስደተኞች ልትሰጥ ነው
አዲስ አበባ፣ መስከረም 24፣ 2016(ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ የመጀመሪያ የሆነውን የዲጂታል መታወቂያ ለስደተኞች ልትሰጥ መሆኑን የስደተኞችና ከስደት ተመላሽ ኮሚሽን አስታወቀ።
ለስደተኞች የብሄራዊ የዲጂታል መታወቂያ ለመስጠት የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ፊርማ በኮሚሽኑ፣ በብሄራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ጽ/ቤትና በተመድ የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽን መካከል ነገ እንደሚፈረም ተመላክቷል።
የዲጂታል መታወቂያ አገልግሎት ባለፉት ሦስት ዓመታት በኢትዮጵያ የሙከራ ትግበራ ላይ የሚገኝ ሲሆን፥ በ2015 ዓ.ም የዲጂታል መታወቂያ አዋጅ ጸድቆ ወደ ሥራ መግባቱ ይታወሳል።
እስከ አሁንም ከ3 ሚሊየን በላይ ዜጎች ብሔራዊ መታወቂያ ለማግኘት የሚያስችላቸውን ምዝገባ ማድረጋቸውን ጽህፈት ቤቱ መግለጹን የዘገበው ኢዜአ ነው።
የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ጽህፈት ቤት በሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት 90 ሚሊየን ዜጎችን የብሔራዊ መታወቂያ ባለቤት ለማድረግ እየሰራ እንደሚገኝ መረጃዎች ያመለክታሉ።
እቅዱ የተፈናቀሉ ዜጎች፣ ሰብአዊ እርዳታ የሚያሻቸውና ሌሎች ማንነታቸውን የሚያረጋግጥ መረጃ ማቅረብ የማይችሉ ዜጎችን ታሳቢ ማድረጉም ተነግሯል።
#Ethiopia #ID #UN
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!