Fana: At a Speed of Life!

ኮሚሽኑ በኢሬቻ በዓል አከባበር ወቅት አደጋ እንዳይከሰት በቂ ዝግጅት ማድረጉን አስታወቀ

 

አዲስ አበባ፣ መስከረም 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በነገዉ ዕለት በአዲስ አበባ የሚከበረዉ የኢሬቻ በዓል ያለምንም አደጋ ተከብሮ እንዲጠናቀቅ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት አጠናቆ ወደስራ መግባቱን አስታወቀ፡፡

በዚህም በበዓሉ ስፍራ ከሚኖር ሰፊ የህዝብ ቁጥር አንጻር በሚኖር መገፋፋትና ሌሎች ድንገተኛ የጤና ዕክሎች ቢያጋጥሙ ፈጣን ምላሽ ለመስጠት ከአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ጋር በትብብር እየተሰራ እንደሚገኝም ተተቁሟል፡፡

በስፍራውም የአንቡላንስና የቅድመ ሆስፒታል ህክምና አገልግሎቶችን የሚሰጡ የጤና ባለሞያዎችም መሰማራታቸው ነው የተገለፀው።

በሌላ በኩል በዓሉ በሚከበርበት ስፍራ የእሳት አደጋ መቆጣጠር ቡድን ፈጣን ምላሽ ለመስጠት በሚያስችል ሁኔታ በሶስት አቅጣጫ አስፈላጊዉ ጥበቃ የሚደረግ ሲሆን÷ ኮሚሽንኑ በዓሉ በሰላም እንዲከበር ከተቋቋመዉ ግብረ ኃይል ጋርም በትብብር እየሰራ ይገኛል ነው የተበለው፡፡

ለእሳትና ለሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች እንዲሁም ለአንቡላንስ አገልግሎቶች በ939 ወይም በ011-1-55-53-00 ፈጥነዉ በማሳወቅ አገልግሎት ማግኘት እንደሚቻል መገለፁን የኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በተመሳሳይ የበዓሉ ታዳሚዎች በዓሉን ያለምንም የትራንስፖርት አቅርቦት ችግር እንዲያከብሩ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በጥምረት እየሰራ መሆኑን የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ አስታውቋል።

ቢሮው በአምስት በሮች እንግዶችን በመቀበል በጀሞ3፣ በቃሊቲ ቶታል፣ ቱሉ ዲምቱ፣ የካ ጣፎ፣ አየር ጤና፣ አዲሱ ገበያና ሳንሱሲ የከተማ አውቶብስ፣ የፐብሊክ ሰርቪስ፣ የታክሲና ሀይገር ተሸከርካሪዎችን በበቂ መጠን ለማቅረብ የቅድመ ዝግጅት ስራውን እንዳጠናቀቀ ገልጿል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.