ኢጋድ የሱዳን ሴቶች በሀገራቸው ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን ለሚያደርጉት አስተዋጽዖ ድጋፍ እንደሚያደርግ ገለፀ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ)የሱዳን ሴቶች በሀገራቸው ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን ለሚያደርጉት አስተዋጽዖ ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልጿል፡፡
የኢጋድ ዋና ጸሃፊ ወርቅነህ ገበየሁ(ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ፥ ለሱዳን ሴቶች ያለኝን ያልተቋረጠ ድጋፍ ዛሬ ”በሱዳን ዘላቂ ሰላም ለማስፈን የሴቶችን አመራር ማሳደግ” ጉባዔ ላይ አካፍያለሁ ብለዋል።
አክለውም ፥ አስደናቂ ጥንካሬያቸው እና የመቋቋም አቅማቸው የሚበረታታ ነው ሲሉ አድናቆታቸውን ገልጸዋል፡፡
አስቸኳይና ቅድሚያ የሚሰጧቸውን ጉዳዮች ለመፍታት አፋጣኝ እና ሁሉን አቀፍ የተቀናጀ እርምጃ እንዲወሰድ መጠየቁንም ነው ያነሱት፡፡
በዚህም የሀገሪቱን ሴቶች የእውነተኛ ሰላም ፈጣሪዎች ናቸው ሲሉም ገልጸዋቸዋል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!