የኢትዮጵያን የአየር ክልል በብቃት መጠበቅ የሚያስችል አየር ኃይል መገንባቱ ተመላከተ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 24 ሰዓት የኢትዮጵያን አየር ክልል በአስተማማኝ ሁኔታ መጠበቅ የሚያስችል አየር ኃይል መገንባቱን የአየር መከላከያ መሣሪያዎች ጥገና መምሪያ አስታወቀ፡፡
የመምሪያው ኃላፊ ኮሎኔል ተሾመ ባጫ እንደገለጹት÷ አሁን ላይ የአየር ኃይሉ የማድረግ አቅም ከመቼውም ጊዜ በላይ ከፍ ብሏል፡፡
አየር ኃይሉን በዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችና በሰለጠነ የሰው ኃይል በማደራጀት ረገድ አበረታች ሥራ መከናወኑንም ነው ያመላከቱት፡፡
ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ የአየር ኃይሉን ግዳጅ የመፈጸም አቅም ከፍ ለማድረግ የተከናወኑ ሥራዎች ተጨባጭ ለውጥ አምጥተዋል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
የኢፌዴሪ አየር ኃይል በዘመናዊ ትጥቅና ብቁ የሰው ኃይል በመታገዝ ከመቼውም ጊዜ በላይ የኢትዮጵያ አየር ክልል አስተማማኝ ዘብ ሆኖ መገንባቱን ኃላፊው አረጋግጠዋል፡፡
አየር ኃይሉ የታጠቃቸውን መሣሪያዎች በመጠገን በአግባቡ ጥቅም ላይ እንዲውሉ ማድረግ የሚያስችል ብቁ የሰው ኃይል ማፍራቱንም አመላክተዋል፡፡
በአየር ኃይል የራዳር ጥገና ባለሙያ ሲቲክ ምትኩ ፈንታ በበኩላቸው÷ አየር ኃይሉ ዘመኑን የሚመጥኑ ራዳሮችን በመጠቀም የኢትዮጵያን አየር ክልል በአስተማማኝ ሁኔታ እየጠበቀ ነው ብለዋል፡፡
በተለይም ዲጂታል ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ረገድ እጅግ አመርቂ ሥራ ተከናውኗል ነው ያሉት፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!