በአዳሚ ቱሉ ወረዳ በደረሰ የመኪና አደጋ የ7 ሰዎች ህይወት አለፈ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በምስራቅ ሸዋ ዞን አዳሚ ቱሉ ወረዳ ውስጥ በደረሰ የመኪና አደጋ የሰባት ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡
አደጋው የደረሰው ከአዳሚ ቱሉ ወረዳ ወደ ባቱ ከተማ ሲጓዝ የነበረ ዳማስ ተሽከርካሪ እና በተቃራኒ አቅጣጫ ሲጓዝ የነበረ ቪ ኤይት (v8) መኪና ገርቢ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ በመጋጨታቸው የተከሰተ መሆኑን የባቱ ከተማ ኮሙኒኬሽን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ገልጿል፡፡
በአደጋው የአራት ሰዎች ሕይወት ወዲያውኑ ሲያልፍ እንዲሁም ሦስት ሰዎች ወደ ሕክምና ተቋም ከተወሰዱ በኋላ ሕይወታቸው ማለፉ ተገልጿል፡፡
ሌሎች በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ታውቋል፡፡
በፌቨን ቢሻው