Fana: At a Speed of Life!

የሱዳን ተፋላሚ ሃይሎች የሠላም ድርድር በጅዳ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሱዳን ጦር እና የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ሃይሎች የሠላም ድርድር በጅዳ ዳግም መጀመሩን የሳዑዲ ዓረቢያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

የሠላም ድርድሩ በአሜሪካ፣ ሳዑዲ ዓረቢያ፣ በምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ድርጅት እና በአፍሪካ ሕብረት አሸማጋይነት ነው እየተካሄደ የሚገኘው፡፡

አሸማጋዮቹ ተፋላሚ ሃይሎች በተኩስ አቁም እና በሌሎች ጉዳዮች ሰፊ መግባባት ላይ እንዲደርሱ በትኩረት እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡

ከዚህ ቀደም ስምምነት የተደረሰባቸውን የሰብዓዊ ሥራን ለማመቻቸትና ዜጎችን ወደ መደበኛ ሕይወት መመለስ የተመለከቱ ጉዳዮች ተፈፃሚ እንዲሆኑ ተፈላሚ ሃይሎች ሥምምነት ላይ እንደሚደርሱም ይጠበቃል፡፡

በግጭቱ የንጹሃን ዜጎችን ሕይወት ለመታደግና ግጭቱ የሚያስከትለውን ተጨማሪ ቀውስ ማስቀረት የሚስያስችል ስምምነት እንደሚፈጠር በድርድሩ ተስፋ መጣሉንም ተመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.