አቶ አወል አርባ በአዋሽ ፈንታሌ የልማት ሥራዎችን ጎበኙ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ በአዋሽ ፈንታሌ ወረዳ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል፡፡
በጉብኝታቸውም በአካባቢው እየለማ የሚገኘውን የፓፓዬ ምርት እና ሌሎች ሥራዎችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል፡፡
አቶ አወል በጉብኝቱ ወቅት እንዳሉት÷ የሕብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተጀመሩ የልማት ሥራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ፡፡
ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ለመተካት የሚደረገው ጥረት አበረታች እንደሆነም በማህበራዊ ትሥሥር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡