Fana: At a Speed of Life!

አንቶኒ ብሊንከን ከፍልስጤም ፕሬዚዳንት ማህሙድ አባስ ጋር ተገናኝተው መከሩ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በፍልስጤም ራማላህ የሚገኙት የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ከፍልስጤም ፕሬዚዳንት ማህሙድ አባስ ጋር ተገናኝተው መከሩ።

የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማቲው ሚለር እንዳስታወቁት፤ በጋዛ እየተደረገ ያለው ሰብዓዊ ድጋፍ እንዳይቋረጥ አሜሪካ በቁርጠኝነት እንደምትሰራ አንቶኒ ብሊንከን አረጋግጠዋል።

በተጨማሪም ፍልስጤማውያን እንዳይፈናቀሉ አሜሪካ የምትሰራ መሆኗን እንደገለጹ ቃል አቀባዩ አስታውቀዋል።

ከዚህ በተጨማሪም በዌስት ባንክ ሰላም እንዲሰፍን እየተደረገ ባለው ጥረት ዙሪያ የመከሩት ባለስልጣናቱ፤ በፍልስጤማውያን ላይ እየደረሰ ያለው ጥቃት በሚቆምበት ሁኔታ ላይ መክረዋል።

አሜሪካ የፍልስጤማውያንም ሆነ የእስራኤላውያን መብት እኩል እንዲጠበቅ መስራቷን የምትቀጥል መሆኗንም ብሊንከን መግለጻቸውን ዘ ዊክና አናዶሉ ዘግበዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.