Fana: At a Speed of Life!

የፈረንሳይ አምባሳደር የጌዴኦ ባህላዊ መልክዓ ምድርን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የፈረንሳይ አምባሳደር ሬሚ ማረሾ የጌዴኦ ባህላዊ መልክዓ ምድርን ጎበኙ።

በጉብኝቱ የኢትዮጵያ ቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ፕሮፌሰር አበባው አያሌው፣ የጌዴኦ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዝናቡ ወልዴ (ዶ/ር) እንዲሁም የዞኑ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎች እንግዶች መገኘታቸውን የዞኑ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

የፈረንሳይ የጥናትና ምርምር ማዕከል የጌዴኦ ታሪካዊ የትክል ድንጋዮች መካነ ቅርስ ምርምርና ጥናት እያካሄደ መሆኑ ይታወቃል፡፡

የጌዴኦ ባህላዊ መልክዓ ምድር በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) ዕውቅና አግኝቶ የዓለም ቅርስ ሆኖ ባለፈው መስከረም ወር መመዝገቡ ይታወሳል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.