Fana: At a Speed of Life!

ልጆቻችን የኢትዮጵያን ችግሮች ለመፍታት ቁልፍ የሆነውን እውቀት መገብየታቸው ተስፋ ሰጭ ነው – ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ህዳር 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) “ልጆቻችን የኢትዮጵያን ችግሮች በሰው ሰራሽ አስተውሎት በመታገዝ ለመፍታት ቁልፍ የሆነውን እውቀት መገብየታቸው ተስፋ ሰጭ ነው” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በማህራዊ ትስስር ገጻቸው÷ በዛሬዉ እለት በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንሰቲትዩት በመገኘት ለሁለት  ወራት ስለሰው ሰራሽ አስተውሎት  ቴክኖሎጂ ምንነት እና ጠቀሜታ ስልጠና ተከታትለው የተመረቁ የነገ ሀገር ተረካቢ ወጣቶችን ተመልክቻለሁ ብለዋል፡፡

ልጆቻችን የኢትዮጵያን ችግሮች በሰው ሰራሽ አስተውሎት በመታገዝ ለመፍታት ቁልፍ የሆነውን እውቀት መገብየታቸው ተስፋ ሰጭ ነው ሲሉም ገልጸዋል፡፡

በልጆቹ አቅም በመገረም የኢትዮጵያን እድገት ለማረጋገጥ እንደሚችሉም ሙሉ እምነት አለኝ ብለዋል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.