Fana: At a Speed of Life!

የገጠር መሬትን ጥቅም እንዲሰጥ ለማድረግ ልዩ ትኩረት መስጠት እንደሚያስፈልግ ተጠቆመ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የገጠር መሬትን ጥቅም እንዲሰጥ ለማድረግ ልዩ ትኩረት መስጠትና በተሻለ መንገድ ማስተዳደር እንደሚያስፈልግ የህዝብ ተወካዮች ምክር አባላት አሳሰቡ፡፡

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 5ኛ መደበኛ ስብሰባውን የተለያዩ ረቂቅ አዋጆችን ተመልክቶ ለሚመለከታቸው ቋሚ ኮሚቴ በመምራት አካሂዷል።

በመደበኛ ስብሰባውም ከተመለከታቸው አጀንዳዎች መካከል የገጠር መሬት አስተዳደር እና አጠቃቀም ረቂቅ አዋጅ አንዱ ነው፡፡

በረቂቅ አዋጁ ሃሳባቸውን የሰጡት የምክር ቤቱ አባላት አዋጁን በዝርዝር የሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ የግብርናውን ዘርፍ ማሳደግ በሚቻልበት ሁኔታ እንዲመለከተው አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

እንዲሁም ፍትሃዊ የገጠር መሬት ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ በሚቻልበት ልክ ሊመለከተው እንደሚገባም አባላቱ አሳስበዋል፡፡

ምክር ቤቱ በዛሬው አጀንዳው የግል ዳታ ጥበቃ ረቂቅ አዋጅን እና የልዩ ኢኮኖሚ ዞን ረቂቅ አዋጅን በመመልከት ለዝርዝር እይታ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ መርቷል፡፡

ምክር ቤቱ የገጠር መሬት አስተዳደር እና አጠቃቀም ረቂቅ አዋጅን በመመልከትም ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ መርቷል፡፡

በይስማው አደራው

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.