Fana: At a Speed of Life!

በኢስትለንደንና ኪንግ ዊልያም ታውን ከኢትዮጵያ ዳያስፖራ አባላት ጋር ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ አፍሪካ ኢስትለንደንና ኪንግ ዊልያም ታውን ከሚገኙ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አባላት ጋር በዜጎች መብትና ደህንነት ማስጠበቅ እንዲሁም በልማት ተሳትፎ ዙሪያ ውይይት ተካሒዷል፡፡

በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሙክታር ከድር (ዶ/ር) የተመራ የልዑካን ቡድን አባላት በኢስተርንኬፕ-ፕሮቪንስ፤ ኢስትለንደን፣ ኪንግ ዊልያም ታውን እንዲሁም በአካባቢው ከሚገኙ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አባላት ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም ÷በዜጎች ደህንነት፣ በዳያስፖራው የልማት ተሳትፎ እንዲሁም በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮችን ላይ መክረዋል፡፡

ኤምባሲው በዜጎች መብትና ጥቅም ማስጠበቅ፣ በዳያስፖራ የልማት ተሳትፎ ዙሪያ እያከናወናቸው ስላሉ ስራዎች እንዲሁም በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ገለጻ አድርጓል፡፡

በአካባቢው የሚገኙ ዜጎች አደረጃጀት በመፍጠር እያጋጠማቸው ያሉትን ችግሮችን ለመፍታት ከኤምባሲው እና ከአካባቢው ማህበረሰብ እንዲሁም የአስተዳደር አካላት ጋር በመቀናጀት እየተንቀሳቀሱ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

የተጀመረው ጥረትም ተጠናክሮ እንዲቀጥልም መጠየቁን የኤምባሲው መረጃ ያመላክታል፡፡

በተለይም በተለያዩ የወንጀል እንቅስቃሴዎች እየተሳተፉና በዜጎችች የሥራና ደህንነት ሥጋቶችንና ችግሮችን እየፈጠሩ የሚገኙ ዜጎች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ተጠይቋል፡፡

በኢትዮጵያ በአንዳንድ አካባቢዎች በሕገወጥ ቡድኖች አማካኝነት በዜጎች የንግድ መደብሮች ላይ የሚፈጸሙ ድርጊቶችን ለመከላከል ከሥራ ሃላፊዎች ጋር ተቀናጅቶ መንቀሳቀስ እንደሚያስፈልግም ተጠቁሟል፡፡

መንግስት በውጭ ለሚኖሩ የዳያስፖራ አባላት በሀገር ቤት በተለያዩ የልማት ዘርፎች እንዲሳተፉ በፖሊሲ የተደገፈ አሰራሮችን ዘርግቶ እያበረታታና እያስፈጸመ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡

ዳያስፖራው ዕድሎቹን በመጠቀምና ተሳትፎውን በማጠናከር ራሱንና ሀገሩን ተጠቃሚ እንዲያደርግም ጥሪ ቀርቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.