Fana: At a Speed of Life!

በደሴ ከተማ በ788 ሚሊየን ብር የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች እየተከናወኑ ነው

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በዘንድሮ በጀት ዓመት ለነባርና አዲስ ለሚገነቡ የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎች 788 ሚሊየን ብር መመደቡን የደሴ ከተማ አስተዳደር መንገዶች ባለስልጣን ገለጸ።

የደሴ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ከበደ መሃመድ እንደገለጹት÷ ከተማ አስተዳደሩ 788 ሚሊየን ብር በመመደብ የመንገድ ግንባታ ስራዎች እንዲከናወኑ እያደረገ ነው፡፡

በበጀት አመቱ  7 ነጥብ 84 ኪሎ ሜትር ነባር መንገድ አስፋልት የማልበስ እንዲሁም 1 ነጥብ 78 ኪሎ ሜትር አዲስ መንገድ ጠጠር የማልበስ ስራ እየተከናወነ ነው ብለዋል፡፡

የልማት ስራዎችን ለማከናወን ማህበረሰቡ ተባባሪ መሆኑን ጠቅሰው÷ በቀጣይም በገንዘብ፣ በእዉቀትና በጉልበት እንዲያግዝ ጥሪ አቅርበዋል።

በሙሉቀን አበበ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.