Fana: At a Speed of Life!

96 ዜጎች ከሊባኖስ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

 

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በተለያዩ ምክንያቶች የመኖሪያና የሥራ ፈቃድ ሳይኖራቸው በሊባኖስ ረዥም ዓመታት ሲኖሩ የነበሩ 96 ሰነድ አልባ ዜጎች በሁለተኛው የበረራ ፕሮግራም ወደ ኢትዮጵያ ዛሬ ተመልሰዋል፡፡

በቀጣይም ሶስተኛውና 89 ዜጎች ወደ ሀገር ቤት የሚመለሱበት የበረራ ፕሮግራም ነገ እንደሚካሄድ ከቤይሩት የኢፌዲሪ ቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በቤይሩት የኢፌዲሪ ቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤት የዜጎች መብትን በማስከበር ሂደት ለተባበሩት ሁሉ ምስጋና አቅርቧል፡፡

በተለያዩ ምክንያቶች የመኖሪያና የሥራ ፈቃድ ሳይኖራቸው በሊባኖስ ረዥም ዓመታት ሲኖሩ የነበሩ ሰነድ አልባ ዜጎችን በጥያቄያቸው መሠረት ያለ እሥር ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ጥያቄው ለሊባኖስ ኢሚግሬሽን ቀርቦ በመጀመሪያው የበረራ ፕሮግራም 78 ዜጎች መመለሳቸው ይታወሳል፡፡

በተመሳሳይ 90 መደበኛ ያልሆኑ ፍልሰተኞች ከጅቡቲ ወደ ኢትዮጵያ ዛሬ ገብተዋል፡፡

ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር በየቀኑ የዜጎችን ህይወት እየቀማ በመሆኑ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ከማህበረሰብ ጋር በመሆን መስራት ያስፈልጋል ሲል በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መልዕክቱን አስተላልፏል፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.