Fana: At a Speed of Life!

በክልሉ የሚገኙ አቅሞችን በአግባቡ በመጠቀም የተጀመሩ ስኬቶችን ማስቀጠል ይገባል- አቶ ጥላሁን ከበደ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የሚገኙ እምቅ አቅሞችን በአግባቡ በመጠቀም የተጀመሩ ስኬቶችን ማስፋትና ማስቀጠል ይገባል ሲሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ገለጹ፡፡

በየደረጃው የሚገኙ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አመራሮች የክልሉን ሠላምና ልማት በጋራ ማጠናከር በሚቻልበት አግባብ ላይ በወላይታ ሶዶ ከተማ እየመከሩ ነው፡፡

የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ÷ በወላይታ ሶዶ ከተማ የተካሄደው የክልሉ ይፋዊ ሥራ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር በሠላም እንዲጠናቀቅ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።

በክልሉ የሚገኙ እምቅ አቅሞችንና የሰው ሃይልን በአግባቡ በመጠቀም የተጀመሩ ስኬቶችን ማስፋትና ማስቀጠል እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

ይህም ጊዜ የማይሰጣቸው የሕዝብ የልማት ፍላጎቶችን ለማረጋገጥ አስቻይ አቅም እንዳለው ማንሳታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

በውይይት መድረኩ ከፌዴራል እስከ ወረዳ እና ከተማ የሚገኙ የክልሉ ተወላጅ አመራሮች እየተሳተፉ እንደሚገኙ ተጠቁሟል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.